የማክሰኞዉን የፓርላማ ዉሎ አላየሁትም ነበር። ብቸኛው
የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ንግግራቸውን ሲጨርሱ "እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን በበረከት ይጎብኛት"
በማለታቸው አፈ ጉባኤዉን አባ ዱላን ጨምሮ የፓርላማ አባላቱ እንደሳቁ የሚያሳየዉን ቪድዮ ሳይ እጅጉን ነበር
ያዘንኩት ግራም ተጋባው። የ እግዚአብሔር ስም መጠራቱ እንዲህ የሚያስቅ ከሆነ እነርሱ የሚያመልኩት ምን ይሆን? የ
እኛ ሀገር መሪዎች ስልጣኔ ነት መስሏቸው ነው እንዳልል ያደጉ አገራት መሪዎች ከንግግር በኃላ እግዚአብሔር
ሀገራችንን ይባርክ ብለው ሲናገሩ አንድም ቀን ሰው ሲስቅ አይቼ አላቅም። ታዲያ ምን የሚሉት ይሆን የ እኛ ሀገር
መሪዎች እንዲህ ድዳቸው እስኪታይ መሳቃቸው ከምን የመነጨ ነው? እኔ ግን በማመን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንን እና
ህዝቦቻን ይባርክ እላለው አሜን እስቲ እናንተም ይሄንን ሺድዮ ተመልከቱ