20111225
ቅድስት ማርያም ግብጻዊት
የኢየሩሳሌም ሊቀፓፓስ ሳፍሮኒዮስ እንደጻፈው:- ቅድስት ማርያም ግብጻዊት የተወለደችው በግብጽ ነዉ::ከዚያም የዝሙት ፍቅር አድርባት:ለ17 አመት ያህል ሰዎችን በሚያቃጥል የኃጥያት እሳት ታስፈጃቸው ነበር ዝሙት እየሰራች:ብዙዎችንም ታስት ነበር:: ዝሙት ከመውደዷ የተነሳ ገንዝብ እንኳን ልስጥሽ ሲሉ አትቀበልም ነበር:: በእግዚአብሔርም አታምንም ነበር በዛው ፋንታ እንደፈለገች ትሆን ነበር:: በልቧ ከዚህ ስራዬ ማንም አይከለክለኝም ትል ነበር:: አንድ ቀን ሊቢያውያን እና ግብጻውያን ወደ ባህር እየተቻኮሉ ሲሄዱ አይታ ወዴት እንደሚሄዱ ብጠይቃቸው የከበረ የጌታችንን መስቀል በዓል ለማክበር ወደ እየሩሳሌም እንደሚሄዱ ሲነግሯት እና የሚሄደው ሰው ብዙ መሆኑን ስታይ: ብዙ ዘመዶችን አገኛለው ብላ ከእነርሱ ጋር ለመሄድ ተነሳች:ለጉዞዋ ወይም ለምግብ የሚሆን አንድም ገንዘብ አልያዘችም ነበር:: በኃላም በሰውነቷ ማማር ብዙዎችን በዝሙት ምክንያት አጠመደች ወደ ተቀደሰ ቦታ የሚሄዱቱን ሰዎች በማሳት ዋና የሰይጣን መረብ ሆና ነበር:: በዚህም ስራዋ እየተኩራራች ለሰው ሁሉ ትናገር ነበር:የሐጥያተኛን ሞት የማይወድ እግዚአብሔር መመለሷን እየጠበቀ ይታገሳት ነበር:: በመጨረሻም እየሩሳሌም ደርሰው ከበዓሉ በፊት እንደለመደችው እንደውም በከፋ መልኩ ዝሙትን አብዝታ ትሰራ እና ሰውንም ታስት ነበር:: የበዓሉ ዕለት ጠዋት ብዙ ተሳላሚዎች ጌታችን መቃብር ላይ ወደ ተሰራችው ቤተ-ክርስቲያን ሊሳለሙ ሲሄዱ አየችና እዛ ሄደው ምን እንደሚያደርጉ ለማወቅ ፍላጎት አደረባት እናም ህዝቡ በሚገቡበት በር እየተጋፋች ለመግባት ትሞክር ጀመር በኃላም በሩ ጋር ስትደርስ የሆነ ሐይል ሲገፋት ይታወቃት ጀመር ሌሎቹን ሰዎች ስታይ በቀላሉ ሲገቡ ታያለች መጀመሪያ ላይ ምንድን ነው እያለች ትስቅ ነበር ደጋግማ ስትሞክር አልቻለችም በኃላም ዝም ብላ በሩ ላይ ቆመች እንደገናም ደጋግማ ሞከረች ልትገባ ግን አልቻለችም !! ሲደክማት ብላ ከበሩ አጠገብ ቆመች በህሊናዋም በብዙ መከራ ምን እንደሆነ ታስብ ጀመር:: ቅዱስ መስቀሉን ለማየት እርሷ ያልቻለችበትን ምክንያት ታስብ ጀመር:የድህነት ቃል የልቦናዋን አይኖች ነካቸው እንዳልገባ የከለከለኝ የራሴ ሃጥያት ስትል አሰበች (ተረዳች):: በኃላም በማልቀስ እና ደረቷን እየደቃች ከውስጣዊ ልቧማዘን ጀመረች:: "ለምን አልገባም? እንዳልገባ የከለከለኝ የኃጢአቴ ብዛት ነውን?" እያለች ደጋግማ እራሷን ትጠይቅ ጀመር:: ያን ግዜ የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማሪያምን ስዕል ከበሩ ላይ አየችና ሄዳ ስዕሉ ፊት ቆማ የስዕሉን ግርማና ውበት ባየች ግዜ ያለፈ የእራሷ ሃጥያት ወለል ብሎ ታያት እና አፈረች::ከዚህም በኃላ በብዙ ለቅሶ ከ ቅድስት ድንግል ማሪያም ስዕል ስር ወድቃ "ከእንግዲህ በኃላ ለጌታየ አገልጋይ ለአንቺም ባርያ እሆን ዘንድ እድል አገኝ ይሆን ?" እያለች ታለቅስ እና ትለምን ጀመር:ጌታችንንም ካለችበት ስቃይና መከራ እንዲያድናት እና በመንገዱ እንዲመራት ለመነችው:"ቅዱስ መስቀሉን ካየው በኃላ አለም እና ደስታዋን እንደምክድ ቃል ገባለው" ብላ ቃል ገባች:: ከጸለየችም በኃላ የመተማመን ስሜት ተሰማትና ወደ መስቀሉ ቦታ ወደሚያስገባው ቦታ ሄደች ከዚያም ያለችግር ገባች በኃላም መስቀሉ ጋር ደርሳ በመንቀጥቅጥ እና በብዙ እምባ ሳመች የእግዚአብሔርን ሚስጥር እና ንስሃን እንዴት እንደሚቀበል አየች:: ከዚያም ወጣ ቃል ወደ ገባችበት ወደ እመቤታችን ስዕል ጋር ሄዳ "የኃጥአንን ንሰሐ ባንቺ አማላጅነት የሚቀበል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!! አሁን የገባውትን ቃል እፈጽም ዘንድ ግዜው ነው እጄን ይዘሽ ወደ ንስሃ ምሪኝ" አለች:: ያን ግዜ የእመቤታችን ስዕል አፍ አውጥታ "ዮርዳኖስን ብትሻገሪ እረፍት ታገኛለሽ" አለቻት:ከዛም እመቤቴ ሆይ አትተዪኝ ብላ አለቀሰች እና ከዚያ ተነስታ ወደ በረሃው ጉዞ ጀመረች ከመንገዶኞቹም አንዱ እህቴ ሆይ እንኪ ብሎ 3 ሳንቲም ሰጣት እና በእነርሱ ለመንገዷ የሚሆን ዳቦ ገዝታ እያለቀሰች ከከተማው ወጣች:መንገድ ላይም መሸባትና የዮሃነስ መጥምቅ ቤት-ክርስቲያን አግኝታ እዛው ስታለቅስ አደረች:: ጠዋትም አስቀድሳ እመቤታችንንም አንቺ ተከተይኝ እያለች ጉዞዋን ጀመረች ጀልባም ፈልጋ ዮርዳኖስን ተሻገረች ከዚያም ወደ አንድ በረሃ ደረሰች:: በዚያም እህልም ሰውም ሳታገኝ ለ47 አመታት እየተጋደለች ወደሱ የሚመለሱትን ከሚቀበል ፈጣሪ ጋር ኖረች::
ከ47 አመትም ከዚህ በኋላ ዞሲማስ የተባለ መነኮስ እመቤታችን አነሳስታ ልካው ቢሄድ ከሩቅ አያት :: ዕርቃኗን ነበረችና ተነስታ ሮጠች :: (እጅግ ከመክሳቷ የተነሳም ሰው መሆኗ አያስታውቅምም ነበር ):: ዞሲማስም ያየሁት ምንድነው ? በረከት ቀረብኝ ብሎ ተከትሏት ሮጠ :: ጥቂት ተሯሩጠውም ወደ ጉድጓድም ገባች :: መለስ ብላም "ከእኔ ጋር ልትነጋገር ከወደድክ እርቃኔን ነኝና ጨርቅ ጣልልኝ " አለችው :: እርሱም መደረቢያውን ጣለላት :: ያንን ለብሳ ወጥታ እጅ ተነሳሱ :: ስላሳለፈችው እና ስለነበራት ህይወት አጫወተችው:ከዛም ለመጀመሪያው 17 አመታት የነበረባትን ፈተና እንዲ አለችው ""አባት ዞሲማስ ሆይ 17 አመት በዚ በረሃ ከአራዊት ከክፉ ምኞት እና ከክፉ ህሊና ጋር ስታገል ኖርኩ:ያለፈ ህይወቴንና ያሳለፍኩትን ደስታ እያሰብኩ እፈተን ነበር:ከረሃብ እና ከውሃ ጥም እንዲሁም ከጸሃይ ሃሩር የተነሳ በጣም ተሰቃይቻለው: ብዙ ግዜ እታመምና ለሞት እደርስም ነበር: ጌታዬም እንዲረዳኝ እለምነው ነበር ህሊናየን መጀመሪያ ወደ ተቀበለችኝ እመቤቴም ስዕል እሄድና እማጸናት ነበር ከዛም በኃላ በ4ቱ ማእዘን የሚያበራ ብርሃን አይ ነበር""እያለችና ሌላም ሌላም ትነግረው ነበር:ከዛም ቅድስት ማሪያም ግብጻዊት በብዙ ተጋድሎ ሰይጣንን ድል ነስታ ቅዱስ ዞሲማሲን በሚቀጥለው አመት ወደዚ በረሃ ስትመጣ የጌታችንን ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን በዕለተ "ፀሎተ-ሃሙስ" ይዘህልኝ በዮርዳኖስ ባህር ዳር እንገናኝ አለችው ና ተመልሳ ወደ በረሃው ገባች በአመቱን ቅዱስ ዞሲማስ ይዞላት መቶ የዮርዳኖስ ባህርን እየተራመደች ስትመጣ ግዜ አይቶ እግዚአብሄርን እያመሰገነ ቅዱስ ስጋውንና ክቡር ደሙን አቀበላት ከዚያም እንደገና ቅዱስ ዞሲማስን አሰናበተችውና በሚቀጥለው አመት እንዲመጣ ነገረችው በኃላም በዓመቱ ሲመጣ አጣት እና እጂግ አለቀሰ ከዚያም ፈልጎ እሬሳዋን አገኘውና ስሟን ባለማወቁ ሲጸጸት ጊዜ አንድ ብጣቂ ወረቀት አገኘና አነበባት "" አባት ዞሲማስ ሆይ በጸሎተ ሃሙስ ማታ ከቅዱስ ሚስጥር ከተቀበልኩ በኃላ ወደ አምላኬ ሄጃለው የደካማይቱን የማርያምን ስጋ በዚህ ቦታ ቅበረው ዓፈር ወደ ዓፈር ይመለስ ዘንድግድ ነው እና ስለ እኔም ጸልይልኝ ስሟን በማወቁ ደስ እያለው እዛው ቀበራት እና ወደ ቤቱ ተመለሰ:: ቅድስት ማርያም ግብጻዊት ያረፈችው በሚያዚያ 6,522ዓ.ም. ነው:: በረከቷ ረድኤቷ በሁላችን ላይ ይደር !! አሜን !!!!
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
nmd
ReplyDeleteyeezy shoes
golden gooses outlet
vans outlet
yeezy shoes
curry 6
bape hoodie
coach outlet
outlet golden goose
kyrie 5
xiaofang20191223