20111227

ቅዱስ ገብርኤል


ታህሳስ 19 ቀን በዚህ ቀን ሰለስቱ ደቂቅ "የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶኑ ሊያድነን ይችላል" ያሉበት ዕለትና ቅዱስ ገብርኤል ከእሣት ያዳቸው ዕለት መታሰቢያ በዓል ነው። ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ነገሩ እንዲህ ነው። ዘመኑ ጣኦት የሚመለክበት ንጉስ ናቡከደነፆር የእግዚአብሔር ሰዎች የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች የነበሩት ወጣቶች ሥም አናንያ (ሲድራቅ) ፤ አዛርያ (ሚሣቅ) ፤ ሚሣኤል (አብድናጎ) ነበሩ። ት/ዳንኤል 3፡1-30 ታሪኩ እንደሚግረን ንጉስ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶ ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሣት ውስጥ ይጣላል ብሎ አወጀ። በዚህ መካከል ሰልስቱ ደቂቅ ነበሩ። የንጉስ ትህዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣኦቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር። የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ ፤ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻል?" ባላቸው ጊዜ የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶን ሊያድነን ይችላል ባያድነንም እንኳን አንተ ለመታመልከው ጣኦት አንሰግድም አሉት ። በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሣት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው የጣሉቸው ወታደሮች የእሣቱ ወላፈን አቃጠላቸው ሠልስቱ ደቂቅን ግን መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አበረደላቸው አጠፋላቸው ። በዚህም ጊዜ ንጉስ ናቡከደነፆር እንዲህ በማለት መሰከረ "እኛ አስረን የጣልናቸው ሦስት ነበሩ አሁን ግን አራተኛው ሰው በእሳቱ ሲመላለስ ይታየኛል እንዲያውም የአማልክትን ልጆች ይመስላል " አለ። የእግዚአብሔር የማዳኑ ስራ ሲገለጥ ቅዱስ ገብርኤል ሲታይ አዋጁ ሁሉ ተሻረ ጉልበት ሁሉ ለጣኦት ተብሎ የነበረው "ጉልበት ሁሉ ለሰልስቱ ደቂቅ አምላክ ይስገድ ይንበርከክ" ተባለ ይህን ሁሉ ታህሳስ 19 ቀን ሆነ በዚህም ምክንያት በታላቅ ደስታ እናከብረዋለን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የመላእክት የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃው ረድየት በረከቱ አይለየን

3 comments: