20120820

ሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ

አንቀጽ 17
·              ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ
1.    ፓትርያርኩ በሞት ሲለይ ወይም በዚህ ሕግ አንቀጽ 16 መሠረት ከሥልጣኑ ሲወርድ ቅዱስ ሲኖዶስ በሹመት ቀደምትነት ካላቸው ሊቃነ ጳጳሳት መካከል በዕለቱ ዐቃቤመንበረ ፓትርያርክ መርጦ ይሾማል፡፡ የተተኪው ፓትርያርክ ምርጫም ይካሔዳል፡፡
2.    የተተኪው ፓትርያርክ ምርጫ አፈጻጸም እንደጊዜውና እንደሥራው ሁኔታ እየታየ 40 እስከ 80 ቀን ባለው ጊዜ ይሆናል፡፡
3.    የዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ተግባር
ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ጊዜያዊ ጉደዮችን ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር እየመከረ ያከናውናል፡፡
በፓትርያርኩ ምርጫ ጊዜም የቅዱስ ሲኖዶስ ሊቀ መንበር ሆኖ ምርጫውን ያስፈጽማል፤ እርሱ ግን ከምርጫው አይገባም::

ምንጭ፦ ሕገ ቤተ ክርስቲያን 1991 .
.

2 comments:

  1. የቤተክርስቲያን ኣባቶች እባካችሁን በአለም ውስጥ የሰለቸንን ፖለቲካ መድረክ አገኘን ብላችሁ ከእግዚአብሄር ቃል ጋር እየቀላቀላችሁ አትስበኩን እኛ ወደ ቤተክርስቲያን የምንመጣው የእግዚአብሄርን ቃል ልንሰማ ነው እንጂ ፖለቲካውንማ የሬድዮውም የቴሌቪዥኑ ጩሀት እሱ ስለሆነ ከዚያ መስማት እንችላለን ሰለ እግዚአብሄር ብላችሁ ህዝቡን ባትፈሩ እግዚአብሄርን ፍሩ ፡፡

    ReplyDelete