20101016

በ እኛ ነዋየተ ቅዱሳን የመናፍቃን ጭፈራ

የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።

የማቴዎስ ወንጌል7፥15

ዛሬ ይህን ለመጻፍ ያስገደደኝ ትላንት አንድ ጋደኛዬ ኢትዮ ትዩብ በሚለው ድህረ ገጽ ላይ የወጣዉን ምስለ ድምጽ ( http://www.ethiotube.net/video/8669/Yetsidiq-Tsehay-Ethiopian-Gospel-Singers%EF%BB%BF ) መናፍቅኑ ከዚህ በፊት በ ቅድስት ቤተክርስትያናችን ላይ ያልሆኑ ስብከቶችን እና የ እኛ የ ሆኑ የዘማ እቃዎችን በመጠቀም ሲዘፍኑ አይተናል በዚም አላበቁም ከ 4 እና 5 አመታት በፊት ዉዳሴማሪያምን ቀየር አድርገዉ ዘመን ባፈራዉ የድምጽ መሳሪያ በመጠቀምን ሲዘፍኑም አይተን አልፈናል የቅርብ ጊዘዉን ላስታዉሳቹ አንድ በልመና የሚተዳደር ሰዉን በገንዘብ ይሁን በሃይ በማስፈራራት አቡነ ያሬድ ነኝ ብሎ የሃሰትምስክርነት እንዲሰጥ ተደገ ይህንንም በዝምታ አለፍን.ለ ኢትዮጲያ ድህነት ተጠያቂዎ የ ኦርቶዶክስ በተክርስትያን ናት ሲሉም አድምጠን አልፈናል

እዚህ ላይ ሳልጠቅስ ማለፍ የማልፈልገዉ ነገር የ መምህር ዘበነን እዉነትን የማዉጣት ስራ ሊበረታታ ይገባዋል . የ ሃይማኖት መሪዎቻችንም በዚህ ነገር ላይ መላ ቢሉ ጥሩ ነው እላለው

ይሄን ቪድዮ ከሌላዉ ለየት የሚያደርገዉ የከበሮዉ፣ የፀናጽሉ፤ የመቋሚያው አላንስ ብሎ መፆረ መስቀሉን፣ጽናውን፣ ቃጭሉን ይዘዉ ሲጨፍሩ አየን ይህንንስ በዝምታ ማለፍ ያለብን አይመስ ለኝም. አባቶቻችን ያቆይልንን የዜማ መሳሪያዎችን እና ንዋያተ ቅዱሳቱን ይዘው ሲጨፍሩ ዝም ካልን የሚቀትለዉ ታቦትን ይዘዉ ይሆናል የሚጨፍሩት.

የቀደሙት አባትኦቻችን ያቆዩልንን ኦርቶዶስ ተዋህዶን እኛም ከ የዜማ መሳሪያዎቻቻን እና ንዋያተ ቅድሳቱ ከሙሉ ሚስጥርና ትርጉማቸው ለሚቀጥለው ትውልድ ማስተላለፉ የእኛ ሀላፊነት ነው።

ተኩላዉ ለምድ ለብሶ በርግጥ መጣል እና

አምላክ ሆይ አድነን ፍጠን ተሎ ና

20101006

እንኳን ለዘመነ ጽጌ በስላም አደረስን

ጌታ ሲወለድ ሰብአ ሰገል «የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት አለ? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንስግድለት መጥተናል» እያሉ በኮከብ እየተመሩ በመጡ ጊዜ በይሁዳ በገሊላና በሰማርያ የሮማውያን ተወካይ የነበረው ንጉሥ ሄሮድስ የጌታችን ንግሥና ምድራዊ ንግሥና መስሎት መንግስቴን ሊቀማኝ ነው ብሎ ደነገጠ፡፡ ፊሪሳውያን «መሲህ ተወልዶ ከሮማውያን አገዛዝ ነጻ ያወጣናል፡፡» ብለው ያምኑ እንደነበር ስለሚያውቅም ይህ የተፈጸመ መስሎት ጭንቀቱ በረታ፡፡ የተወለደውን ሕፃንም ለመግደል ተነሳ፡፡
ስለዚህም ሰብአ ሰገልን አስጠርቶ «ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔም እንድሰግድለት ወደ
እኔ ተመልሳችሁ ያለበትን ንገሩኝ» በማለት በሽንገላ ተናገራቸው፡፡
ጠቢባኑም ከሄሮድስ ከተለዩ በኋላ በኮከቡ እየተመሩ ጉዞአቸውን ቀጥለው ጌታችንን ከእናቱ ጋር አገኙት ፤ ተንበርክከው ሰገዱለት፤ ወርቅ ፣ ዕጣን፣ ከርቤ እጅ መንሻ አቀረቡለት፡፡
የእግዚአብሔር መልአክ ወደ ሄሮድስ እንዳይመለሱ ነገር ግን መንገድ ቀይረው ወደ ሀገራቸው እንዲሄዱ በነገራቸው መሠረት በሌላ መንገድ ወደ መጡበት ተደብቀው ተመለሱ፡፡
«እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ «ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነስ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሸ እስክነግርህም በዚያ ተቀመጥ አለው፡፡ » /ማቴ. 2 13 14/.......ዮሴፍም ተነሣ በዕድሜዋ በጣም ልጅ የነበረችው እመቤታችን ገና የተወለደውን ሕፃን አቅፋ የምትቀመጥበት አህያም ተዘጋጀ፡፡
ጉዞአቸውን ጀመሩ........
በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ዘመነ ጽጌ ወርኃ ጽጌ ይባላል:: ይኸውም ተራሮችን ሸንተረሮችን በአበባ ያስጌጠ ሰማይን በከዋክብት ያጌጠ ምድርን በስነ ጽጌያት ያሸበረቀ አምላክ ነው እና:: እሱ የሚመሰገንበት ስለሆነ .....ሌላው ጽጌ የተባለች እናቱ ድንግል ማርያም ፍሬ የተባለ ልጇ እሱን ኢየሱስ ክርስቶስን አዝላ ከኢየሩሳሌም ምድረ እስራኤል ወደ ግብጽ እንዲሁም ወደ አገራችን ኢትዮጵያ የተሰደደችበትን በማሰብ ለአርባ ቀናት ያህል ምዕመናን በፈቃዳቸው ለበረከት ይፆማሉ:: ሊቃውንቱም ከምሽቱ ሶስት ሰዓት እስከ ንጋቱ አስራ ሁለት ሰዓት ድረስ «ጽጌ ጽጌ ዘሰሎሞን ወዳዊት ጽጌ አሮን ዘክህነት» እያሉ ያመሰግኗታል:: እመቤታችንም በስደቷ ወራት ብዙ መከራ ደርሶባታል ተርባለች ተጠምታለች ልጄን ይገሉብኛል ብላ ተጨንቃለች::
ጌታ ወደ ግብጽ የተሰደደው ለምንድን ነው ቢሉ?....
(አንደኛ)..ነቢዩ ኢሳያስ የተናገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ነው:: «ወይወርድ እግዚእነ ተጽእኖ ድበ ደመና ቀሊል» «ጌታችን በፈጣን ደመና ሆኖ ወደ ግብጽ ይወርዳል» ኢሳያስ 19 ቁ. 1
(ሁለተኛ).. በግብጽ አምልኮተ ጣኦት ብዝቶ ነበር እና አምልኮተ ጣኦትን ለማጥፋት ነው::
እመቤታችን ሶስት አመት ከስድስት ወር እስኪፈጸም ድረስ በብግጽ እናም በሀገራችን በኢትዮጵያ የስደት ጊዜ አሳልፋለች ማቴ..2 ቁ. 19
በስደት ከቆዩ በኋላ ሄሮድስ ሞተ።.....ሄሮድስም ከሞተ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በግብጽ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ «የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ አለው፡፡ እርሱም ተነስቶ ሕጻኑንና እናቱን ይዞ ወደ እስራኤል ሀገር ገባ» ማቴ 2-19-21/
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመስከረም 26 ቀን ጀምሮ እስከ ኅዳር 6
ቀን ድረስ የጌታን እና የእመቤታችንን ስደት በማሰብ የጽጌ ፆም ይፆማል
እንኳን አደረሳችሁ!!!

20101001

ስለ ጽዮን ዝም አልልም፥


ስለ ጽዮን ዝም አልልም፥ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፥ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ።አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ፤ የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ።በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል፥ በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ።ምዕራፍ 62:1-3
መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ። ደስ ይበልሽ፥ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ አላት።እርስዋም ባየችው ጊዜ ከንግግሩ በጣም ደነገጠችና። ይህ እንዴት ያለ ሰላምታ ነው? ብላ አሰበች።መልአኩም እንዲህ አላት። ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።ሉቃ 1፤28-30 መልአኩ ገብርኤል እንዳመሰገናት እኛስ ብናመሰግናት ብንዘምርላት ክብራን ለ አለም ብንመሰክር ስተታቺን ምኑ ላይ ነው ?
ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች። አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ፥ የሰላምታሽ ድምጽ በጆሮዬ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና።ከጌታ፤ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብፅዕት ናት። የሉቃስ ወንጌል 1:41-45
ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፥ በውስጥዋም ሰው ተወለደ እርሱ ራሱም ልዑል መሠረታት።መዝሙረ ዳዊት 87:5
ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።መዝሙረ ዳዊት 129:5
የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ የእግዚአብሔርም ከተማ፥ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻልትንቢተ ኢሳይያስ 60:14